20250814_105710

ብጉር

ብጉር
ምንነት: በብዙ ምክንያት የቆዳ ቀዳዳወች ሲደፈኑ በሚመጣ የቆዳ መቆጣት የሚመጣ ችግር ነው::
ምክንያቶች:

  • የፊት ቆዳ ቅባት መብዛት እና የቆዳ ቀዳዳዎችን መድፈን
  • ለአቅመ አዳም ወይም ሄዋን ሲደረስ የሚመነጭ አንድሮጅን ሆርሞን መብዛት
  • ፒ. አክኔ የሚባል ባክቴሪያ
  • ቤተሰብ ተመሳሳይ ችግር መኖር
  • ጣፋጭ እና ወተት ያላቸው ምግቦች ያስብሳሉ
  • የተለያዩ የፊት ቅባቶች እና ኮስሞቲክሶች ያስብሳሉ
    ከጠቅላላው ህዝብ 85% የሚሆነው በዕድሜው በሆነ ጊዜ በብጉር ይያዛል::
    ምልክቶች
    ማሳከክ የሌለው ሽፍታ: መግል የሚይዙ ሽፍታወች ወይም ዕባጮች
    በብዛት ብጉር ፊት ላይ: ደረት ወይም ጀርባ ላይ ይወጣል
    ሴቶች ላይ ሆርሞናል ብጉር ከሆነ የወር አበባ መዛባት: ፊት ላይ ፀጉር መብዛት: የድምፅ መወፈር
    ህክምና
  • የተለያዩ የሚቀቡ እና የሚዋጡ መድሀኒቶች አሉ
  • የሚወጡትን ሽፍታወች በዕጅ አለመነካካት
  • ፊትን የሚሸፍኑ ቅባቶች: ኮስሞቲክሶች: እና የፊት ማስክ አለመጠቀም
  • የፊትን ቅባት በተለያዩ የብጉር ሳሙናወች እና መታጠቢያወች መቀነስ
  • በገላ እና በተለይ በልብስ ሳሙና ፊትን አለመታጠብ
  • ፀሀይ መከላከል
  • የመጨረሻ ደረጃ ላይ ከደረሰ አይሶትሪትኖይን የሚባል የሚዋጥ መድሀኒት ያስፈልገዋል:: አይሶትሬቲኖይን ፍቱን የሆነ የብጉር መድሀኒት ሲሆን በክሊኒካችን ማግኘት ይችላሉ።
  • ብጉር ሲድን የሚተወው ጠባሳ ክሊኒካችን ቢመጡ በማይክሮ ኒድሊንግ እንዲሁም በደርማአብሬዥን መታከም ይችላል::
    ዶ/ር ዳዊት ዮሐንስ
    የቆዳና የአባላዘር ቺፍ ስፔሻሊስት
    አድራሻ ቦሌ ቡልቡላ ማርያም ማዞሪያ ፀሀይ ህንፃ
    ስልክ 0912050354

ቦቶክስ

ቦቶክስ
የቦቶክስ ህክምና ለሚከተሉት ችግሮች ፍቱን መፍትሄ ነው።
– ከዕድሜ ጋር ወይም በመኮሳተር ወይም በመሳቅ ለሚመጡ የፊት ቆዳ መስመሮች
– ላብ ለሚያስቸግረው በተለይ ዕጅ ላይ: እግር ላይ: ብብት ላይ እና ፊት ላይ
በክሊኒካችን ቢመጡ ይህንን አገልግሎት ያገኛሉ።

Screenshot_20250730_205542_Telegram

የቆዳ ኪንታሮት

ኪንታሮት(wart)

  • Human papiloma virus በሚባሉ ቫይረሶች ይከሰታል
  • በብዛት ዕድሜያቸው ከ5_20 ያሉ ሰወች ላይ ይከሰታል
  • የበሽታ መከላከል አቅማቸው የቀነሰ ሰወች ላይ ደግሞ የመከሰት ዕድሉ ይጨምራል በተለይ አዋቂወች ላይ
  • በብዛት የሚወጡት ዕጅ ላይ: ጣት ላይ እና ጥፍር አካባቢ ነው
    ህክምና
  • የሚቀመሙ መድሀኒቶች
  • በፈሳሽ ናይትሮጅን (cryotherapy) ማጥፋት
  • በኤሌክትሮካውተሪ (electrocautery) ማሽን ማጥፋት
  • ወደ ክሊኒካችን ቢመጡ በዘመናዊ electrocautery እና cryotherapy ማሽኖቻችን እናጠፋልዎታለን::
    ዶ/ር ዳዊት ዮሀንስ
    የቆዳና የአባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት
    ጥላ የቆዳና የአባላዘር ልዩ ክሊኒክ
    አድራሻ ቦሌ ቡልቡላ ማሪያም ማዞሪያ ፀሀይ ህንፃ
    ስልክ 0967253625 ወይም 0912050354
Screenshot_20250626_120822_Facebook

የጥፍር ቆዳ ውስጥ ገብቶ ማደግ

ingrown nail(የጥፍር ቆዳ ውስጥ መግባት)
👉 በብዛት የሚከሰተው የእግር አውራጣት ጥፍር ላይ ቢሆንም ማንኛውንም ጥፍር ሊያጠቃ ይችላል
ምክንያቶች
👉 ጠባብ ጫማ ማድረግ እና ጥፍርን በአግባቡ ያለመቁረጥ ዋናወቹ ናቸው
👉 በተጨማሪም አደጋ እና ጥፍር ከጣት አኳያ ትልቅ ከሆነ ሊያስከትሉ ይችላሉ
ምልክት
👉 መቅላት ማበጥ እና ህመም ይኖረዋል
👉 ኢንፌክችን ፈጥሮ መግል ሊይዝ ይችላል
ህክምና
👉 ሞቅ ባለ ውሀ ለተወሰኑ ደቂቃወች በቀን ከ3-4 ጊዜ መዘፍዘፍና ማድረቅ
👉 ምቾት ያለው ጠባብ የሆነ ጫማ ማድረግ
👉 የህመም ማስታገሻ መውሰድ
👉 ጥፍሩን ቀስ አርጎ አንስቶ በጥፍሩ እና በቆዳው መሀል ጥጥ መጨመር:: ጥጡን በየቀኑ መቀየር
👉 እንደ መጨረሻ አማራጭ በቀዶ ህክምና ማስወጣት። ክሊኒካችን ቢመጡ በቀላሉ በቀዶ ጥገና ይስተካከላል
ዶ/ር ዳዊት ዮሀንስ
የቆዳና የአባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት

1000006867

ከመጠን ያለፈ ላብ

አስደሳች ዜና ላብ ለሚያስቸግረው
ከመጠን ያለፈ ላብ (hyperhydrosis)

  • ከሙቀት ወይም እንቅስቃሴ ጋር የማይገናኝና በብዛት በማላብ ልብስን ወይም እጅን በላብ መዝፈቅ ነው
    ምክንያቶች
  • ከልጅነት ጀምሮ እስከ 24 ዓመት የሚከሰት ከሆነ ያለ ምንም ምክንያት ሊከሰት ይችላል
  • ከ30- 50 % ጊዜ በቤተሰብ ተመሳሳይ ችግር ሊኖር ይችላል
  • ከ25 ዓመት ቡሀላ የሚከሰት ከሆነ ግን ብዙ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ
    _ የስኳር ህመም ኤች አይ ቪ
    _ ቲቢ በተለይ ላቡ ማታ የሚብስ ከሆነ
    _ የታይሮይድ እና አድሬናል ዕጢ ችግር
    _ ማረጥ
    _ የልብ ህመም አንዳንድ ካንሰሮች
    _ የነርቭ በሽታ ወይም መጎዳት
    _ መድሀኒቶች በተለይ ለድብርት ለህመም ማስታገሻ የሚሰጡ
    አይነቶች
  • እጅ እግር ብብት ወይም ፊት ላይ የተወሰነ ሊሆን ይችላል
    _ ብዙ ጊዜ ያለ ምንም ምክንያት ይከሰታል
  • ሙሉ ሰውነት ላይ ሊከሰት ይችላል
    _ ከላይ ከተዘረዘሩት አንዱ ሊያመጣው ይችላል
    ህክምና
  • የሚቀባ የሚቀመም እና የሚዋጡ መድሀኒቶች አሉ
  • አልሙኒየም ያላቸው ዲዎድራንቶችን መጠቀም
  • ቅመማቅመም ሽንኩርት የበዛበት ምግብ መቀነስ በተለይ ከላቡ ጋር ሽታ ካለ
  • ካፌይን ያላቸው እንደ ሻይ ቡና መቀነስ
  • ሰውነትን ቶሎ ቶሎ መታጠብ
  • ከጥጥ የተሰሩ እና ቀለል ያሉ የሚያናፍሱ ልብሶችን መልበስ
  • በአዮንቶፎረሲስ በሚባል መሳሪያ ላብን ማከም
  • በክሊኒካችን ቢመጡ በዘመናዊ iontophorosis ማሽን የብብት የእጅ እና የእግር ላብዎትን እናክምዎታለን።
    ዶ/ር ዳዊት ዮሀንስ
    የቆዳና የአባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት

Screenshot_20250208_122140_Facebook

የብጉር ጠባሳ

የብጉር ጠባሳ (acne scar)

  • ብጉር በጊዜው ሳይታከም ቀርቶ ለሚፈጠር ጠባሳ በmironeedling እና prp በአንድ ላይ በመጠም ህክምና መስጠት መጀመራችንን በደስታ እንገልፃለን
    ዶ/ር ዳዊት ዮሀንስ
    የቆዳና የአባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት
    ጥላ የቆዳና የአባላዘር ህክምና ልዩ ክሊኒክ
    አድራሻ ቦሌ ቡልቡላ ማሪያም ማዞሪያ ፀሀይ ህንፃ ስልክ 0912050354 / 0967253625
Screenshot_20250114_110938_Chrome

አልማዝ ባለጭራ

አልማዝ ባለጭራ(Herpes zoster)
ጉድፍ የሚባል በብዛት ልጆችን የሚያጠቃ ቯሪሴላ ዞስተር በተባለ ቯይረስ የሚከሰት ህመም ሲድን ነርቭ ውስጥ ተደብቆ ይቆይና ሰውነታችን በሚጎዳበት ጊዜ ቫይረሱ በድጋሚ ተመልሶ ተባዝቶ ሲወጣ አልማዝ ባለጭራ ያመጣል::
አጋላጭ ነገሮች

  • በኤች አይ ቪ ወይም በሌሎች ምክንያቶች የበሽታ መከላከል ዐቅም መቀነስ
  • የዕድሜ መግፋት በተለይ ከ60 ዐመት ብሀላ
  • ሴት ፆታ
  • ጭንቀት ወይም stress
  • አልኮል መጠቀም ማብዛት
  • የወጣበት ቦታ ላይ ቀደም ብሎ ኦፕራሲዮን ተደርጎ ወይም አካላዊ ጉዳት ደርሶ ከሆነ
  • 20 % የሚሆነው ያለምንም አጋላጭ ነገር ሊከሰት ይችላል
    ምልክቶች
  • በብዛት ውሀ የቋጠሩ አንዳንዴም ያልቋጠሩ አንድ ቦታ ላይ ሰብሰብ ያሉ ትንንሽ ሽፍታወች
  • ሽፍታወቹ የሚወጡት ከሰውነታችን መሀል አካፋይ በግራ ወይም በቀኝ በኩል ሆኖ የሰውነታችንን መሀል አያቓርጡም
  • ውጋት ወይም ማቃጠል ያለው ከባድ ህመም በተለይ ዕድሜያቸው የገፋ ሰወች ላይ ይብሳል
    ህክምና
  • በልምድ ወይም በባህል ዘመናዊ ህክምና በሽታውን ይደብቀዋል የሚባለው የተሳሳተ አመለካከት ነው
  • ሽፍታው በሂደት በራሱ ቢጠፋም አሳይክሎቪር የሚባል ፀረ- ቫይረስ መድሀኒት መውሰድ ቶሎ እንዲጠፋ ያደርገዋል
  • በዋናነት ትኩረት ተሰጥቶ መታከም ያለበት በሽታው የሚያመጣው የውጋት ህመም ነው
  • የተለያዩ የነርቭ ህመምን የሚያስታግሱ በተለምዶ ከምንጠቀምባቸው የህመም ማስታገሻወች ለየት ያሉ መድሀኒቶች ከ1 ወር – 3 ወር መወሰድ አለባቸው ዶ/ር ዳዊት ዮሀንስ የቆዳና የአባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት ጥላ የቆዳና የአባላዘር ልዩ ክሊኒክ ስልክ 0967253625 / 0912050354
DSC_0557

የቆዳ አስም

የቆዳ አስም

  • በብዛት የሚታይ የቆዳ መቆጣት እና የውስጥ አለርጂ ሲሆን ብዙ ጊዜ ገና በልጅነት ዕድሜ ይጀምራል
  • ከአጠቃላይ ህዝብ 20 % የሚሆነው በዚህ ህመም ሊጠቃ ይችላል
    ምክንያቶች/አባባሽ ነገሮች
  • በዘር መጋለጥ
  • በታማሚው ወይም በቅርብ ቤተሰብ ላይ አስም ወይም ሳይነስ ሲኖር
  • በተፈጥሮ ደረቅ እና ቶሎ የሚቆጣ ቆዳ ሲሆን
  • በዋናነት ያለምንም ምክንያት የሚከሰት የውስጥ አለርጂ ሲሆን እንደ እንቁላል: ወተት እና ለውዝ
    የመሳሰሉ ምግቦች አልፎ አልፎ ሊያባብሱት ይችላሉ
  • ቶሎ ቶሎ መታጠብ
  • በጠንካራ ሳሙናወች በተለይ በልብስና በዕቃ ሳሙናወች መታጠብ
  • ቀዝቃዛ እና ደረቅ አየር (የበጋ ወቅት)
  • የሚኮሰኩሱ ልብሶች
  • ላብና ሙቀት
  • ኢንፌክሽኖች
    ምልክቶች
  • ከፍተኛ የሆነ ማሳከክ
  • ጥፍት ምልስ ማለት
  • ደረቅ ቆዳ
  • የቆዳ ሽፍታወች: የቆዳ መቅላት: የቆዳ ማዠት
  • እየቆየ ሲሄድ የቆዳ መወፈር እና መጥቆር
  • ኢንፌክሽን ሲይዝ መግል መፍሰስ
  • ከ2 ዓመት በታች በሆኑ ህፃናት ላይ የሚወጣው ፊት: ጭንቅላት: ጀርባ: እጅ ወይም እግር ላይ ሲሆን
  • ከፍ ያሉ ህፃናት እና አዋቂወች ላይ መተጣጠፊያ ላይ ይወጣል
    ህክምና
  • በሽታው አለርጂ ስለሆነ ሊመላለስ እንደሚችል እና ህመሙን መቆጣጠር እንጂ ሙሉ ለሙሉ ማጥፋት እነደማይቻል ማስረዳት
  • የቆዳ ቅባቶች እንደ ቫዝሊን: ፓራፊን ወይም ሌሎች ኦይሎችን በየቀኑ መቀባት
  • ሰውነት መታጠብን መቀነስ
  • ወዛማ የሆኑ እንደ ዶቭ ወይም ጆንሰን ያሉ ሳሙናወችን ወይም ሻወር ጄል ለገላ መጠቀም
  • ከጥጥ የተሰሩ ለስላሳ ልብሶችን መልበስ
  • ልብስ ከታጠበ ቡሀላ በደንብ ማለቅለቅ
  • ላብና ሙቀት እንዳይፈጥር ልብስ አለመደራረብ
  • የሚያባብሰው ምግብ ካለ ደጋግመን አይተን እርግጠኛ ስንሆን ነው ማቆም ያለብን
  • የቆዳ ሀኪም ጋር ክትትል ማድረግ
  • የተለያዩ የሚቀቡ እና የሚዋጡ መድሀኒቶች ይኖራሉ
  • ኢንፌክሽን ካለ ማከም
  • ለአለርጂ የምንወስዳቸው መድሀኒቶች የጎንዮሽ ጉዳት ስለሚያስከትሉ በሀኪም ትዕዛዝ ብቻ መወሰድ ይኖርባቸዋል
    ዶ/ር ዳዊት ዮሀንስ
    የቆዳና የአባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት
Screenshot_20241224_112433_Telegram

nairobi fly bite

Paederus dermtitis (Nairobi fly dermatitis) (ናይሮቢ ዝንብ ደርማታይተስ ምንድን ነው ?
👉 ናይሮቢ ዝንብ በምትባል ነፍሳት የሚከሰት
     የቆዳ መቆጣት ነው።
👉ነፍሳቷ በምትነካካ ወይም በምትጨፈለቅ ጊዜ
     pederin (ፔድሪን) የተባለ መርዛማ ኬሚካል 
     ትለቃለች ። ይህም ኬሚካል ቆዳን ያስቆጣል።
👉ምልክቱም የቆዳ መቅላት ፣ የማቃጠል ስሜት
     ሲቆይ የቆዳ መጥቆር ፣ መላላጥ ፣መግል
     መያዝ ምልክቶች ይታያሉ ።
👉በግንቦት በሰኔ እና በሐምሌ ወራቶች ላይ
     በብዛት ይከሰታል።
👉የበሰበሰ ቅጠላ ቅጠል መኖሪያ አካባቢ መኖር፣
     መሬት ላይ መተኛት ፣ አጋላጭ ሁኔታዎች
     ሲሆኑ
👉ፀረ ነፍሳት ኬሚካል መርጨት ፣ ሰውነትን
      በሚገባ መሸፈን፣  መከላከያ መንገዶች
      ናቸው።
👉 በፍጥነት ሕክምና ማግኘት የቆዳን መቆጣት
      ከመቀነሱም በተጨማሪ የቆዳ መጥቆርን እና
      ተጨማሪ የባክቴሪያ ኢንፌክሽን ላለመጋለጥ
      ይረዳል ።
ዶ/ር ዳዊት ዮሀንስ
የቆዳና የአባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት
ጥላ የቆዳና የአባላዘር ህክምና ልዩ ክሊኒክ
አድራሻ ቦሌ ቡልቡላ ማሪያም ማዞሪያ ፀሀይ ህንፃ ስልክ 0912050354 / 0967253625