የማህፀን ፈሳሽ
- ሁሉም ሴቶች ላይ በተለይ ለአቅመ ሄዋን ከደረሱ ቡሀላ መጠነኛ የሆነ በማህፀን የሚመጣ ፈሳሽ ይኖራል
- ይህ ፈሳሽ በተለይ በእርግዝና ወቅት: በፆታዊ ግንኙነት ግዜ: የወሊድ መከላከያ እንክብሎች ሲወሰዱ እና የወር አበባ በታየ በ14ኛው ቀን ላይ ይጨምራል
- በዕድሜ ምክንያት የወር አበባ በሚቆምበት ጊዜ ፈሳሹ ይቀንሳል
- ጤናማ ፈሳሽ የሚባለው አነስተኛ (ከ1- 4 ሚ.ሊ) ንፁህ: ውሀ ቀለም ወይም ነጣ ያለ እና ሽታ የሌለው ነው
- ጤናማ ያልሆነ ፈሳሽ ምክንያቱ ብዙ ቢሆንም ዋና ዋናወቹ
*የማህፀን ጫፍ ኢንፌክሽን የሚያመጡ እንደ ጨብጥ የመሳሰሉ እና ሌሎች የአባላዘር በሽታወች
*በፆታዊ ግንኙነት የማይተላለፋ ካንዲዲያሲስ የሚባል ፋንገስ እና ባክቴሪያል ቫጂኖሲስ የሚባሉ ከማህፀን ጫፍ ውጪ የሚከሰቱ ኢንፌክሽኖች
*አልፎ አልፎ ካንሰሮች በተለይ የማህፀን ጫፍ ካንሰር
- የማህፀን ጫፍ ኢንፌክሽን የሚያመጡ እንደ ጨብጥ የመሳሰሉ እና ሌሎች የአባላዘር በሽታወች አጋላጭ ነገሮች
- አዲስ ወይም ብዙ የፆታዊ ግንኙነት ጓደኛ
- ኮንደምን ባግባቡ አለመጠቀም
- አልኮል እና ሌሎች ሱሶችን መጠቀም
- ትዳር ያለመያዝ ወዘተ
ሲሆኑ ምልክታቸው ሽንት ሲሸና ከባድ ማቃጠል: ቢጫ ከለር ያለው ሽታ ያለው በዛ ያለ ፈሳሽ ነው
- በፆታዊ ግንኙነት የማይተላለፋ ካንዲዲያሲስ የሚባል ፋንገስ እና ባክቴሪያል ቫጂኖሲስ የሚባሉ ከማህፀን ጫፍ ውጪ የሚከሰቱ ኢንፌክሽኖች አጋላጭ ነገሮች
- ቶሎ ቶሎ ማህፀንን መታጠብ
- በማህፀን የሚቀመጥ የወሊድ መከላከያ ሲኖር
- ውፍረት
- ፆታዊ ግንኙነት ሲበዛ
- ፀረ ባክቴሪያ መድሀኒቶችን ቅርብ ጊዜ መጠቀም
- ጥብቅ ያለ የውስጥ ልብስ ፖንት አብዝቶ ማረግ
- ስኳር ኤች አይ ቪ እና ሌሎች የሰውነት መከላከያ የሚቀንሱ ህመሞች
- ሲጋራ ማጨስ
_ ላክቶ ባሲለስ በብዛት የማህፀን ፈሳሽ ውስጥ የሚገኝ ባክቴሪያ ሲሆን አሲድ በማመንጨት ሌሎች ጎጂ ተህዋሲያን እንዳይራቡ ያደርጋል
_ ከላይ የጠቀስናቸው አጋላጭ ነገሮች ሲኖሩ ግን የባክቴሪያው መጠን ስለሚቀንስ ሌሎች ጎጂ ባክቴሪያወች ሲራቡ ባክቴሪያል ቫጂኖሲስ የሚባል ጤናማ ያልሆነ ፈሳሽ የሚያመጣ ህመም ይመጣል
_ ምልክቱም ማሳከክ የሌለው ነጣ ቀጠን ያለ የአሳ ሽታ ያለው ፈሳሽ ነው
_ ካንዲዳ አልቢካነስ የሚባል ፋንገስ በተወሰነ ደረጃ መሀፀን ውስጥ ይገኛል
_ ከላይ የጠቀስናቸው አጋላጭ ነገሮች ሲኖሩ ፋንገሱ በብዛት በመራባት ካንዲዲያሲስ የሚባል ኢንፌክሽን ያመጣል
_ ምልክቱም ማሳከክ እና ወፍራም ነጭ እርጎ የመሰለ ፈሳሽ ነው
_ እንደ ማጠቃለያ ጤናማ ያልሆነ የማህፀን ፈሳሽ በሚኖርበት ጊዜ በግንኙነት የሚተላለፍና የማይተላለፍ ሊሆን ይችላል:: ትኩረት መደረግ ያለበት አጋላጭ ነገሮቹ ላይ ነው









