የማህፀን ፈሳሽ
- ሁሉም ሴቶች ላይ በተለይ ለአቅመ ሄዋን ከደረሱ ቡሀላ መጠነኛ የሆነ በማህፀን የሚመጣ ፈሳሽ ይኖራል
- ይህ ፈሳሽ በተለይ በእርግዝና ወቅት: በፆታዊ ግንኙነት ግዜ: የወሊድ መከላከያ እንክብሎች ሲወሰዱ እና የወር አበባ በታየ በ14ኛው ቀን ላይ ይጨምራል
- በዕድሜ ምክንያት የወር አበባ በሚቆምበት ጊዜ ፈሳሹ ይቀንሳል
- ጤናማ ፈሳሽ የሚባለው አነስተኛ (ከ1- 4 ሚ.ሊ) ንፁህ: ውሀ ቀለም ወይም ነጣ ያለ እና ሽታ የሌለው ነው
- ጤናማ ያልሆነ ፈሳሽ ምክንያቱ ብዙ ቢሆንም ዋና ዋናወቹ
*የማህፀን ጫፍ ኢንፌክሽን የሚያመጡ እንደ ጨብጥ የመሳሰሉ እና ሌሎች የአባላዘር በሽታወች
*በፆታዊ ግንኙነት የማይተላለፋ ካንዲዲያሲስ የሚባል ፋንገስ እና ባክቴሪያል ቫጂኖሲስ የሚባሉ ከማህፀን ጫፍ ውጪ የሚከሰቱ ኢንፌክሽኖች
*አልፎ አልፎ ካንሰሮች በተለይ የማህፀን ጫፍ ካንሰር
- የማህፀን ጫፍ ኢንፌክሽን የሚያመጡ እንደ ጨብጥ የመሳሰሉ እና ሌሎች የአባላዘር በሽታወች አጋላጭ ነገሮች
– አዲስ ወይም ብዙ የፆታዊ ግንኙነት ጓደኛ
– ኮንደምን ባግባቡ አለመጠቀም
– አልኮል እና ሌሎች ሱሶችን መጠቀም
– ትዳር ያለመያዝ ወዘተ
ሲሆኑ ምልክታቸው ሽንት ሲሸና ከባድ ማቃጠል: ቢጫ ከለር ያለው ሽታ ያለው በዛ ያለ ፈሳሽ ነው - በፆታዊ ግንኙነት የማይተላለፋ ካንዲዲያሲስ የሚባል ፋንገስ እና ባክቴሪያል ቫጂኖሲስ የሚባሉ ከማህፀን ጫፍ ውጪ የሚከሰቱ ኢንፌክሽኖች አጋላጭ ነገሮች
– ቶሎ ቶሎ ማህፀንን መታጠብ
– በማህፀን የሚቀመጥ የወሊድ መከላከያ ሲኖር
– ውፍረት
– ፆታዊ ግንኙነት ሲበዛ
– ፀረ ባክቴሪያ መድሀኒቶችን ቅርብ ጊዜ መጠቀም
– ጥብቅ ያለ የውስጥ ልብስ ፖንት አብዝቶ ማረግ
– ስኳር ኤች አይ ቪ እና ሌሎች የሰውነት መከላከያ የሚቀንሱ ህመሞች
– ሲጋራ ማጨስ
_ ላክቶ ባሲለስ በብዛት የማህፀን ፈሳሽ ውስጥ የሚገኝ ባክቴሪያ ሲሆን አሲድ በማመንጨት ሌሎች ጎጂ ተህዋሲያን እንዳይራቡ ያደርጋል
_ ከላይ የጠቀስናቸው አጋላጭ ነገሮች ሲኖሩ ግን የባክቴሪያው መጠን ስለሚቀንስ ሌሎች ጎጂ ባክቴሪያወች ሲራቡ ባክቴሪያል ቫጂኖሲስ የሚባል ጤናማ ያልሆነ ፈሳሽ የሚያመጣ ህመም ይመጣል
_ ምልክቱም ማሳከክ የሌለው ነጣ ቀጠን ያለ የአሳ ሽታ ያለው ፈሳሽ ነው
_ ካንዲዳ አልቢካነስ የሚባል ፋንገስ በተወሰነ ደረጃ መሀፀን ውስጥ ይገኛል
_ ከላይ የጠቀስናቸው አጋላጭ ነገሮች ሲኖሩ ፋንገሱ በብዛት በመራባት ካንዲዲያሲስ የሚባል ኢንፌክሽን ያመጣል
_ ምልክቱም ማሳከክ እና ወፍራም ነጭ እርጎ የመሰለ ፈሳሽ ነው
_ እንደ ማጠቃለያ ጤናማ ያልሆነ የማህፀን ፈሳሽ በሚኖርበት ጊዜ በግንኙነት የሚተላለፍና የማይተላለፍ ሊሆን ይችላል:: ትኩረት መደረግ ያለበት አጋላጭ ነገሮቹ ላይ ነው


https://shorturl.fm/vQq4B
https://shorturl.fm/5V6C8