Screenshot_20241231_180739_Facebook

የማህፀን ፈሳሽ

የማህፀን ፈሳሽ

  • ሁሉም ሴቶች ላይ በተለይ ለአቅመ ሄዋን ከደረሱ ቡሀላ መጠነኛ የሆነ በማህፀን የሚመጣ ፈሳሽ ይኖራል
  • ይህ ፈሳሽ በተለይ በእርግዝና ወቅት: በፆታዊ ግንኙነት ግዜ: የወሊድ መከላከያ እንክብሎች ሲወሰዱ እና የወር አበባ በታየ በ14ኛው ቀን ላይ ይጨምራል
  • በዕድሜ ምክንያት የወር አበባ በሚቆምበት ጊዜ ፈሳሹ ይቀንሳል
  • ጤናማ ፈሳሽ የሚባለው አነስተኛ (ከ1- 4 ሚ.ሊ) ንፁህ: ውሀ ቀለም ወይም ነጣ ያለ እና ሽታ የሌለው ነው
  • ጤናማ ያልሆነ ፈሳሽ ምክንያቱ ብዙ ቢሆንም ዋና ዋናወቹ
        *የማህፀን ጫፍ ኢንፌክሽን የሚያመጡ እንደ ጨብጥ የመሳሰሉ እና ሌሎች የአባላዘር በሽታወች
        *በፆታዊ ግንኙነት የማይተላለፋ ካንዲዲያሲስ የሚባል ፋንገስ እና ባክቴሪያል ቫጂኖሲስ የሚባሉ ከማህፀን ጫፍ ውጪ የሚከሰቱ ኢንፌክሽኖች
        *አልፎ አልፎ ካንሰሮች በተለይ የማህፀን ጫፍ ካንሰር
  1. የማህፀን ጫፍ ኢንፌክሽን የሚያመጡ እንደ ጨብጥ የመሳሰሉ እና ሌሎች የአባላዘር በሽታወች አጋላጭ ነገሮች
           – አዲስ ወይም ብዙ የፆታዊ ግንኙነት ጓደኛ
           –  ኮንደምን ባግባቡ አለመጠቀም
           – አልኮል እና ሌሎች ሱሶችን መጠቀም
           – ትዳር ያለመያዝ ወዘተ
    ሲሆኑ ምልክታቸው ሽንት ሲሸና ከባድ ማቃጠል: ቢጫ ከለር ያለው ሽታ ያለው በዛ ያለ ፈሳሽ ነው
  2. በፆታዊ ግንኙነት የማይተላለፋ ካንዲዲያሲስ የሚባል ፋንገስ እና ባክቴሪያል ቫጂኖሲስ የሚባሉ ከማህፀን ጫፍ ውጪ የሚከሰቱ ኢንፌክሽኖች አጋላጭ ነገሮች
         – ቶሎ ቶሎ ማህፀንን መታጠብ
         – በማህፀን የሚቀመጥ የወሊድ መከላከያ ሲኖር
         – ውፍረት
         – ፆታዊ ግንኙነት ሲበዛ
         – ፀረ ባክቴሪያ መድሀኒቶችን ቅርብ ጊዜ መጠቀም
         – ጥብቅ ያለ የውስጥ ልብስ ፖንት አብዝቶ ማረግ
         – ስኳር ኤች አይ ቪ እና ሌሎች የሰውነት መከላከያ የሚቀንሱ ህመሞች
         – ሲጋራ ማጨስ
    _ ላክቶ ባሲለስ በብዛት የማህፀን ፈሳሽ ውስጥ የሚገኝ ባክቴሪያ ሲሆን አሲድ በማመንጨት ሌሎች ጎጂ ተህዋሲያን እንዳይራቡ ያደርጋል
    _ ከላይ የጠቀስናቸው አጋላጭ ነገሮች ሲኖሩ ግን የባክቴሪያው መጠን ስለሚቀንስ ሌሎች ጎጂ ባክቴሪያወች ሲራቡ ባክቴሪያል ቫጂኖሲስ የሚባል ጤናማ ያልሆነ ፈሳሽ የሚያመጣ ህመም ይመጣል
    _ ምልክቱም ማሳከክ የሌለው ነጣ ቀጠን ያለ የአሳ ሽታ ያለው ፈሳሽ ነው
    _ ካንዲዳ አልቢካነስ የሚባል ፋንገስ በተወሰነ ደረጃ መሀፀን ውስጥ ይገኛል
    _ ከላይ የጠቀስናቸው አጋላጭ ነገሮች ሲኖሩ ፋንገሱ በብዛት በመራባት ካንዲዲያሲስ የሚባል ኢንፌክሽን ያመጣል
    _ ምልክቱም ማሳከክ እና ወፍራም ነጭ እርጎ የመሰለ ፈሳሽ ነው
    _ እንደ ማጠቃለያ ጤናማ ያልሆነ የማህፀን ፈሳሽ በሚኖርበት ጊዜ በግንኙነት የሚተላለፍና የማይተላለፍ ሊሆን ይችላል:: ትኩረት መደረግ ያለበት አጋላጭ ነገሮቹ ላይ ነው
20250814_105710

ብጉር

ብጉር
ምንነት: በብዙ ምክንያት የቆዳ ቀዳዳወች ሲደፈኑ በሚመጣ የቆዳ መቆጣት የሚመጣ ችግር ነው::
ምክንያቶች:

  • የፊት ቆዳ ቅባት መብዛት እና የቆዳ ቀዳዳዎችን መድፈን
  • ለአቅመ አዳም ወይም ሄዋን ሲደረስ የሚመነጭ አንድሮጅን ሆርሞን መብዛት
  • ፒ. አክኔ የሚባል ባክቴሪያ
  • ቤተሰብ ተመሳሳይ ችግር መኖር
  • ጣፋጭ እና ወተት ያላቸው ምግቦች ያስብሳሉ
  • የተለያዩ የፊት ቅባቶች እና ኮስሞቲክሶች ያስብሳሉ
    ከጠቅላላው ህዝብ 85% የሚሆነው በዕድሜው በሆነ ጊዜ በብጉር ይያዛል::
    ምልክቶች
    ማሳከክ የሌለው ሽፍታ: መግል የሚይዙ ሽፍታወች ወይም ዕባጮች
    በብዛት ብጉር ፊት ላይ: ደረት ወይም ጀርባ ላይ ይወጣል
    ሴቶች ላይ ሆርሞናል ብጉር ከሆነ የወር አበባ መዛባት: ፊት ላይ ፀጉር መብዛት: የድምፅ መወፈር
    ህክምና
  • የተለያዩ የሚቀቡ እና የሚዋጡ መድሀኒቶች አሉ
  • የሚወጡትን ሽፍታወች በዕጅ አለመነካካት
  • ፊትን የሚሸፍኑ ቅባቶች: ኮስሞቲክሶች: እና የፊት ማስክ አለመጠቀም
  • የፊትን ቅባት በተለያዩ የብጉር ሳሙናወች እና መታጠቢያወች መቀነስ
  • በገላ እና በተለይ በልብስ ሳሙና ፊትን አለመታጠብ
  • ፀሀይ መከላከል
  • የመጨረሻ ደረጃ ላይ ከደረሰ አይሶትሪትኖይን የሚባል የሚዋጥ መድሀኒት ያስፈልገዋል:: አይሶትሬቲኖይን ፍቱን የሆነ የብጉር መድሀኒት ሲሆን በክሊኒካችን ማግኘት ይችላሉ።
  • ብጉር ሲድን የሚተወው ጠባሳ ክሊኒካችን ቢመጡ በማይክሮ ኒድሊንግ እንዲሁም በደርማአብሬዥን መታከም ይችላል::
    ዶ/ር ዳዊት ዮሐንስ
    የቆዳና የአባላዘር ቺፍ ስፔሻሊስት
    አድራሻ ቦሌ ቡልቡላ ማርያም ማዞሪያ ፀሀይ ህንፃ
    ስልክ 0912050354

ቦቶክስ

ቦቶክስ
የቦቶክስ ህክምና ለሚከተሉት ችግሮች ፍቱን መፍትሄ ነው።
– ከዕድሜ ጋር ወይም በመኮሳተር ወይም በመሳቅ ለሚመጡ የፊት ቆዳ መስመሮች
– ላብ ለሚያስቸግረው በተለይ ዕጅ ላይ: እግር ላይ: ብብት ላይ እና ፊት ላይ
በክሊኒካችን ቢመጡ ይህንን አገልግሎት ያገኛሉ።

Screenshot_20250730_205542_Telegram

የቆዳ ኪንታሮት

ኪንታሮት(wart)

  • Human papiloma virus በሚባሉ ቫይረሶች ይከሰታል
  • በብዛት ዕድሜያቸው ከ5_20 ያሉ ሰወች ላይ ይከሰታል
  • የበሽታ መከላከል አቅማቸው የቀነሰ ሰወች ላይ ደግሞ የመከሰት ዕድሉ ይጨምራል በተለይ አዋቂወች ላይ
  • በብዛት የሚወጡት ዕጅ ላይ: ጣት ላይ እና ጥፍር አካባቢ ነው
    ህክምና
  • የሚቀመሙ መድሀኒቶች
  • በፈሳሽ ናይትሮጅን (cryotherapy) ማጥፋት
  • በኤሌክትሮካውተሪ (electrocautery) ማሽን ማጥፋት
  • ወደ ክሊኒካችን ቢመጡ በዘመናዊ electrocautery እና cryotherapy ማሽኖቻችን እናጠፋልዎታለን::
    ዶ/ር ዳዊት ዮሀንስ
    የቆዳና የአባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት
    ጥላ የቆዳና የአባላዘር ልዩ ክሊኒክ
    አድራሻ ቦሌ ቡልቡላ ማሪያም ማዞሪያ ፀሀይ ህንፃ
    ስልክ 0967253625 ወይም 0912050354

PRP

የPRP ህክምና

  • ይህ ህክምና ለፀጉር መነቃቀል እና መመለጥ, ለፊት ቆዳ መሸብሸብ, ለቆዳ ሸንተረር እና ለጠባሳ በጣም ወሳኝ መፍትሄ ነው
  • PRP: platelate rich plasma ከታካሚው ደም በመውሰድ እና platelate የተባሉትን የደም ሴሎች በመለየት ለታካሚው መልሶ መስጠት ነው
  • platelate የተባሉት የደም ሴሎች ለፀጉር: ለቆዳ እና ለተለያዩ የሰውነታችን ሴሎች ዕድገት የሚሆን ጠቃሚ growth factor ወይም ንጥረ ነገር ስላላቸው ለፀጉር መነቃቀል እና መመለጥን: ለፊት ቆዳ መሸብሸብ: ለሸንተረር ወዘተ አሁን ላይ ሁነኛ መፍትሄ እየሆኑ ይገኛሉ
  • ይህ ህክምና ከፀጉር ንቅለ ተከላ በመቀጠል ለፀጉር ሁነኛ መፍትሄ ነው
  • ክሊኒካችም ይህንን ህክምና በተመጣጣኝ ዋጋ ይዞለዎት መጥቷል
                ዶ/ር ዳዊት ዮሀንስ
              የቆዳና የአባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት
          ጥላ የቆዳና የአባላዘር ህክምና ልዩ ክሊኒክ
    አድራሻ ቦሌ ቡልቡላ ማሪያም ማዞሪያ ፀሀይ ህንፃ