20250814_105710

ብጉር

ብጉር
ምንነት: በብዙ ምክንያት የቆዳ ቀዳዳወች ሲደፈኑ በሚመጣ የቆዳ መቆጣት የሚመጣ ችግር ነው::
ምክንያቶች:

  • የፊት ቆዳ ቅባት መብዛት እና የቆዳ ቀዳዳዎችን መድፈን
  • ለአቅመ አዳም ወይም ሄዋን ሲደረስ የሚመነጭ አንድሮጅን ሆርሞን መብዛት
  • ፒ. አክኔ የሚባል ባክቴሪያ
  • ቤተሰብ ተመሳሳይ ችግር መኖር
  • ጣፋጭ እና ወተት ያላቸው ምግቦች ያስብሳሉ
  • የተለያዩ የፊት ቅባቶች እና ኮስሞቲክሶች ያስብሳሉ
    ከጠቅላላው ህዝብ 85% የሚሆነው በዕድሜው በሆነ ጊዜ በብጉር ይያዛል::
    ምልክቶች
    ማሳከክ የሌለው ሽፍታ: መግል የሚይዙ ሽፍታወች ወይም ዕባጮች
    በብዛት ብጉር ፊት ላይ: ደረት ወይም ጀርባ ላይ ይወጣል
    ሴቶች ላይ ሆርሞናል ብጉር ከሆነ የወር አበባ መዛባት: ፊት ላይ ፀጉር መብዛት: የድምፅ መወፈር
    ህክምና
  • የተለያዩ የሚቀቡ እና የሚዋጡ መድሀኒቶች አሉ
  • የሚወጡትን ሽፍታወች በዕጅ አለመነካካት
  • ፊትን የሚሸፍኑ ቅባቶች: ኮስሞቲክሶች: እና የፊት ማስክ አለመጠቀም
  • የፊትን ቅባት በተለያዩ የብጉር ሳሙናወች እና መታጠቢያወች መቀነስ
  • በገላ እና በተለይ በልብስ ሳሙና ፊትን አለመታጠብ
  • ፀሀይ መከላከል
  • የመጨረሻ ደረጃ ላይ ከደረሰ አይሶትሪትኖይን የሚባል የሚዋጥ መድሀኒት ያስፈልገዋል:: አይሶትሬቲኖይን ፍቱን የሆነ የብጉር መድሀኒት ሲሆን በክሊኒካችን ማግኘት ይችላሉ።
  • ብጉር ሲድን የሚተወው ጠባሳ ክሊኒካችን ቢመጡ በማይክሮ ኒድሊንግ እንዲሁም በደርማአብሬዥን መታከም ይችላል::
    ዶ/ር ዳዊት ዮሐንስ
    የቆዳና የአባላዘር ቺፍ ስፔሻሊስት
    አድራሻ ቦሌ ቡልቡላ ማርያም ማዞሪያ ፀሀይ ህንፃ
    ስልክ 0912050354

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *