file(1)(1)(1)

ፎረፎር

ፎረፎር

  • የቆዳ ወዝ ወይም ቅባት በብዛት ባለበት ቦታ በሚራቡ ፋንገሶች የሚከሰት አለርጂ ነው
  • በብዛት የሚወጣውም ፀጉር: ፊት: ጆሮ እና አንዳንዴም ደረት ጀርባ ወይም ብልት ላይ ነው::
  • ምልክቱም – ማሳከክ – ወደ ቢጫ የሚያደላ የቆዳ ማፈክፈክ – ያዝ መለስ ማለት – የቆዳ መቅላት -የሚከሰተውም
    • አዲስ የተወለዱ ህፃናት ላይ ከሁለት ሳምንት ጀምሮ እስከ ዘጠነኛ ወር ሲሆን ከዛም በራሱ ይጠፋል
    • አዋቂ ላይ ከአቅመ አዳም/ ሄዋን ጀምሮ በማንኛውም እድሜ ይከሰታል
  • የበሽታ መከላከል አቅም ሲደክም በተለይ በኤች አይ ቪ ፎረፎር በብዛት እና ከባድ ሆኖ ይከሰታል
  • ፎረፎርን ከቆረቆር ለመለየት አንዳንዴ ምርመራ ሊያስፈልግ ይችላል
  • ቆረቆር ህፃናትን ከ3- 12 ዓመት ሲያጠቃ ፎረፎር ደግሞ ከ1 ዓመት ያነሱ ህፃናትን እና ከ12 ዓመት በላይ ያሉ ሰወችን ያጠቃል
    ህክምና
  • አለርጂ ስለሆነ ሊመላለስ ስለሚችል አዋቂወች ላይ ክትትል ይፈልጋል
  • የተለያዩ የሚዋጡ: የሚቀቡ: የሚቀመሙ እና ሻምፖወች ይኖራሉ
  • የሚያፈከፍከውን ወይም ልጥፍ ብሎ የወጣውን በእጅ አለመቅረፍ/አለመነካካት
  • ፀጉር ላይ ሲወጣ ፓራፊን ወይም የወይራ ዘይት መቀባት ከዛም በማበጠሪያ ቀስ ብሎ የሚያፈከፍከውን ማንሳት ይቻላል
  • ፀረ ፎረፎር ሻምፖ በሳምንት ከ2-3 ጊዜ ከ10-15 ደቂቃ አቆይቶ መታጠብ
    ዶ/ር ዳዊት ዮሀንስ
    የቆዳና የአባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት
Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *