የፊት ቆዳ መሳሳት(rosacea)
- እስከ 10 % የሚሆኑ ሰወች ላይ ይከሰታል
- መገለጫወቹ የፊት ቆዳ በተለይ ጉንጭ እና አፍንጫ መቅላት ወይም መጥቆር: ማቃጠል: አልፎ አልፎም ሽፍታና መግል ሊይዝ ይችላል
- በብዛት የሚከሰተው ሴቶች ላይ: ቀላ ያለ የቆዳ ቀለም ያላቸው ላይ እና ከ30 ዓመት ቡሀላ ነው
ምክንያቶች - በብዛት ምክንያቱ ላይታወቅ ይችላል
- ፊት በፀሀይ ጨረር ሲጎዳ
- ስቴሮይድ መድሀኒቶች እንደ ደርማላር ደርሞቬት የመሳሰሉትን መቀባት
አባባሽ ነገሮች - ሙቀት: ፀሀይ: የሚያቃጥሉ እና ቅመማ ቅመም የበዛባቸው ምግቦች: አልኮሆል: ንዴት: ንፋስ: የመሳሰሉት
- አልፍ አልፍ ለማድያት ተብሎ የሚቀመሙ መድሀኒቶች ውስጥ የሚጨመሩ መድሀኒቶች
ህክምና - ፀሀይ መከላከል: የፀሀይ መከላከያ እና ጥላ መጠቀም
- የፀሀይ መከላከያ ከኬሚካል ይልቅ ፊዚካል ወይም ሚኒራል ሰን ስክሪን መጠቀም
- ከላይ የተገለፁትን አባባሽ ነገሮች መቀነስ
- በተቻለ መጠን የሚቀባቡ እና ኮስሞቲክስ ነገሮችን መቀነስ
- ሳሙናወችን በተቻለ መጠን መቀነስ እና አልፎ አልፎ መጠቀም
- ፊትን ከሳሙና ይልቅ በክሊንሰር መታጠብ
- የተለያዩ የሚዋጡ: የሚቀቡ እና የሚቀመሙ መድሀኒቶች ይኖራሉ
- በተለይ አዜላይክ አሲድ 15 % ጄል (azelaic acid 15 % gel) በጣም አሪፍ መድሀኒት ሲሆን ብዙ ቦታ ግን አይገኝም እኛ ጋር መጥተው ማግኘት ይችላሉ::
ዶ/ር ዳዊት ዮሀንስ
የቆዳና የአባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት
ጥላ የቆዳና የአባላዘር ልዩ ክሊኒክ
አድራሻ ቦሌ ቡልቡላ ማሪያም ማዞሪያ ፀሀይ ህንፃ
ስልክ 0967253625 ወይም 0912050354

Add a Comment