አልማዝ ባለጭራ(Herpes zoster)
ጉድፍ የሚባል በብዛት ልጆችን የሚያጠቃ ቯሪሴላ ዞስተር በተባለ ቯይረስ የሚከሰት ህመም ሲድን ነርቭ ውስጥ ተደብቆ ይቆይና ሰውነታችን በሚጎዳበት ጊዜ ቫይረሱ በድጋሚ ተመልሶ ተባዝቶ ሲወጣ አልማዝ ባለጭራ ያመጣል::
አጋላጭ ነገሮች
- በኤች አይ ቪ ወይም በሌሎች ምክንያቶች የበሽታ መከላከል ዐቅም መቀነስ
- የዕድሜ መግፋት በተለይ ከ60 ዐመት ብሀላ
- ሴት ፆታ
- ጭንቀት ወይም stress
- አልኮል መጠቀም ማብዛት
- የወጣበት ቦታ ላይ ቀደም ብሎ ኦፕራሲዮን ተደርጎ ወይም አካላዊ ጉዳት ደርሶ ከሆነ
- 20 % የሚሆነው ያለምንም አጋላጭ ነገር ሊከሰት ይችላል
ምልክቶች - በብዛት ውሀ የቋጠሩ አንዳንዴም ያልቋጠሩ አንድ ቦታ ላይ ሰብሰብ ያሉ ትንንሽ ሽፍታወች
- ሽፍታወቹ የሚወጡት ከሰውነታችን መሀል አካፋይ በግራ ወይም በቀኝ በኩል ሆኖ የሰውነታችንን መሀል አያቓርጡም
- ውጋት ወይም ማቃጠል ያለው ከባድ ህመም በተለይ ዕድሜያቸው የገፋ ሰወች ላይ ይብሳል
ህክምና - በልምድ ወይም በባህል ዘመናዊ ህክምና በሽታውን ይደብቀዋል የሚባለው የተሳሳተ አመለካከት ነው
- ሽፍታው በሂደት በራሱ ቢጠፋም አሳይክሎቪር የሚባል ፀረ- ቫይረስ መድሀኒት መውሰድ ቶሎ እንዲጠፋ ያደርገዋል
- በዋናነት ትኩረት ተሰጥቶ መታከም ያለበት በሽታው የሚያመጣው የውጋት ህመም ነው
- የተለያዩ የነርቭ ህመምን የሚያስታግሱ በተለምዶ ከምንጠቀምባቸው የህመም ማስታገሻወች ለየት ያሉ መድሀኒቶች ከ1 ወር – 3 ወር መወሰድ አለባቸው
ዶ/ር ዳዊት ዮሀንስ የቆዳና የአባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት ጥላ የቆዳና የአባላዘር ልዩ ክሊኒክ
ስልክ 0967253625 / 0912050354
Add a Comment