የቆዳ አስም
- በብዛት የሚታይ የቆዳ መቆጣት እና የውስጥ አለርጂ ሲሆን ብዙ ጊዜ ገና በልጅነት ዕድሜ ይጀምራል
- ከአጠቃላይ ህዝብ 20 % የሚሆነው በዚህ ህመም ሊጠቃ ይችላል
ምክንያቶች/አባባሽ ነገሮች - በዘር መጋለጥ
- በታማሚው ወይም በቅርብ ቤተሰብ ላይ አስም ወይም ሳይነስ ሲኖር
- በተፈጥሮ ደረቅ እና ቶሎ የሚቆጣ ቆዳ ሲሆን
- በዋናነት ያለምንም ምክንያት የሚከሰት የውስጥ አለርጂ ሲሆን እንደ እንቁላል: ወተት እና ለውዝ
የመሳሰሉ ምግቦች አልፎ አልፎ ሊያባብሱት ይችላሉ - ቶሎ ቶሎ መታጠብ
- በጠንካራ ሳሙናወች በተለይ በልብስና በዕቃ ሳሙናወች መታጠብ
- ቀዝቃዛ እና ደረቅ አየር (የበጋ ወቅት)
- የሚኮሰኩሱ ልብሶች
- ላብና ሙቀት
- ኢንፌክሽኖች
ምልክቶች - ከፍተኛ የሆነ ማሳከክ
- ጥፍት ምልስ ማለት
- ደረቅ ቆዳ
- የቆዳ ሽፍታወች: የቆዳ መቅላት: የቆዳ ማዠት
- እየቆየ ሲሄድ የቆዳ መወፈር እና መጥቆር
- ኢንፌክሽን ሲይዝ መግል መፍሰስ
- ከ2 ዓመት በታች በሆኑ ህፃናት ላይ የሚወጣው ፊት: ጭንቅላት: ጀርባ: እጅ ወይም እግር ላይ ሲሆን
- ከፍ ያሉ ህፃናት እና አዋቂወች ላይ መተጣጠፊያ ላይ ይወጣል
ህክምና - በሽታው አለርጂ ስለሆነ ሊመላለስ እንደሚችል እና ህመሙን መቆጣጠር እንጂ ሙሉ ለሙሉ ማጥፋት እነደማይቻል ማስረዳት
- የቆዳ ቅባቶች እንደ ቫዝሊን: ፓራፊን ወይም ሌሎች ኦይሎችን በየቀኑ መቀባት
- ሰውነት መታጠብን መቀነስ
- ወዛማ የሆኑ እንደ ዶቭ ወይም ጆንሰን ያሉ ሳሙናወችን ወይም ሻወር ጄል ለገላ መጠቀም
- ከጥጥ የተሰሩ ለስላሳ ልብሶችን መልበስ
- ልብስ ከታጠበ ቡሀላ በደንብ ማለቅለቅ
- ላብና ሙቀት እንዳይፈጥር ልብስ አለመደራረብ
- የሚያባብሰው ምግብ ካለ ደጋግመን አይተን እርግጠኛ ስንሆን ነው ማቆም ያለብን
- የቆዳ ሀኪም ጋር ክትትል ማድረግ
- የተለያዩ የሚቀቡ እና የሚዋጡ መድሀኒቶች ይኖራሉ
- ኢንፌክሽን ካለ ማከም
- ለአለርጂ የምንወስዳቸው መድሀኒቶች የጎንዮሽ ጉዳት ስለሚያስከትሉ በሀኪም ትዕዛዝ ብቻ መወሰድ ይኖርባቸዋል
ዶ/ር ዳዊት ዮሀንስ
የቆዳና የአባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት


Add a Comment