Paederus dermtitis (Nairobi fly dermatitis) (ናይሮቢ ዝንብ ደርማታይተስ ምንድን ነው ?
👉 ናይሮቢ ዝንብ በምትባል ነፍሳት የሚከሰት
የቆዳ መቆጣት ነው።
👉ነፍሳቷ በምትነካካ ወይም በምትጨፈለቅ ጊዜ
pederin (ፔድሪን) የተባለ መርዛማ ኬሚካል
ትለቃለች ። ይህም ኬሚካል ቆዳን ያስቆጣል።
👉ምልክቱም የቆዳ መቅላት ፣ የማቃጠል ስሜት
ሲቆይ የቆዳ መጥቆር ፣ መላላጥ ፣መግል
መያዝ ምልክቶች ይታያሉ ።
👉በግንቦት በሰኔ እና በሐምሌ ወራቶች ላይ
በብዛት ይከሰታል።
👉የበሰበሰ ቅጠላ ቅጠል መኖሪያ አካባቢ መኖር፣
መሬት ላይ መተኛት ፣ አጋላጭ ሁኔታዎች
ሲሆኑ
👉ፀረ ነፍሳት ኬሚካል መርጨት ፣ ሰውነትን
በሚገባ መሸፈን፣ መከላከያ መንገዶች
ናቸው።
👉 በፍጥነት ሕክምና ማግኘት የቆዳን መቆጣት
ከመቀነሱም በተጨማሪ የቆዳ መጥቆርን እና
ተጨማሪ የባክቴሪያ ኢንፌክሽን ላለመጋለጥ
ይረዳል ።
ዶ/ር ዳዊት ዮሀንስ
የቆዳና የአባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት
ጥላ የቆዳና የአባላዘር ህክምና ልዩ ክሊኒክ
አድራሻ ቦሌ ቡልቡላ ማሪያም ማዞሪያ ፀሀይ ህንፃ ስልክ 0912050354 / 0967253625


Add a Comment