ፎረፎር
- የቆዳ ወዝ ወይም ቅባት በብዛት ባለበት ቦታ በሚራቡ ፋንገሶች የሚከሰት አለርጂ ነው
- በብዛት የሚወጣውም ፀጉር: ፊት: ጆሮ እና አንዳንዴም ደረት ጀርባ ወይም ብልት ላይ ነው::
- ምልክቱም – ማሳከክ – ወደ ቢጫ የሚያደላ የቆዳ ማፈክፈክ – ያዝ መለስ ማለት – የቆዳ መቅላት -የሚከሰተውም
- አዲስ የተወለዱ ህፃናት ላይ ከሁለት ሳምንት ጀምሮ እስከ ዘጠነኛ ወር ሲሆን ከዛም በራሱ ይጠፋል
- አዋቂ ላይ ከአቅመ አዳም/ ሄዋን ጀምሮ በማንኛውም እድሜ ይከሰታል
- የበሽታ መከላከል አቅም ሲደክም በተለይ በኤች አይ ቪ ፎረፎር በብዛት እና ከባድ ሆኖ ይከሰታል
- ፎረፎርን ከቆረቆር ለመለየት አንዳንዴ ምርመራ ሊያስፈልግ ይችላል
- ቆረቆር ህፃናትን ከ3- 12 ዓመት ሲያጠቃ ፎረፎር ደግሞ ከ1 ዓመት ያነሱ ህፃናትን እና ከ12 ዓመት በላይ ያሉ ሰወችን ያጠቃል
ህክምና - አለርጂ ስለሆነ ሊመላለስ ስለሚችል አዋቂወች ላይ ክትትል ይፈልጋል
- የተለያዩ የሚዋጡ: የሚቀቡ: የሚቀመሙ እና ሻምፖወች ይኖራሉ
- የሚያፈከፍከውን ወይም ልጥፍ ብሎ የወጣውን በእጅ አለመቅረፍ/አለመነካካት
- ፀጉር ላይ ሲወጣ ፓራፊን ወይም የወይራ ዘይት መቀባት ከዛም በማበጠሪያ ቀስ ብሎ የሚያፈከፍከውን ማንሳት ይቻላል
- ፀረ ፎረፎር ሻምፖ በሳምንት ከ2-3 ጊዜ ከ10-15 ደቂቃ አቆይቶ መታጠብ
ዶ/ር ዳዊት ዮሀንስ
የቆዳና የአባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት


Add a Comment