የማህፀን ፈሳሽ

የማህፀን ፈሳሽ(vaginal dischage)

  • ሁሉም ሴቶች ላይ በተለይ ለአቅመ ሄዋን ከደረሱ ቡሀላ መጠነኛ የሆነ በማህፀን የሚመጣ ፈሳሽ ይኖራል
  • ይህ ፈሳሽ በተለይ በእርግዝና ወቅት: በፆታዊ ግንኙነት ግዜ: የወሊድ መከላከያ እንክብሎች ሲወሰዱ እና የወር አበባ በታየ በ14ኛው ቀን ላይ ይጨምራል
  • በዕድሜ ምክንያት የወር አበባ በሚቆምበት ጊዜ ፈሳሹ ይቀንሳል
  • ጤናማ ፈሳሽ የሚባለው አነስተኛ (ከ1- 4 ሚ.ሊ) ንፁህ: ውሀ ቀለም ወይም ነጣ ያለ እና ሽታ የሌለው ነው
  • ጤናማ ያልሆነ ፈሳሽ ምክንያቱ ብዙ ቢሆንም ዋና ዋናወቹ
    *የማህፀን ጫፍ ኢንፌክሽን የሚያመጡ እንደ ጨብጥ የመሳሰሉ እና ሌሎች የአባላዘር በሽታወች
    *በፆታዊ ግንኙነት የማይተላለፋ ካንዲዲያሲስ የሚባል ፋንገስ እና ባክቴሪያል ቫጂኖሲስ የሚባሉ ከማህፀን ጫፍ ውጪ የሚከሰቱ ኢንፌክሽኖች
    *አልፎ አልፎ ካንሰሮች በተለይ የማህፀን ጫፍ ካንሰር በተለይ ፈሳሹ ከደም ጋር ከተቀላቀለ
  1. የማህፀን ጫፍ ኢንፌክሽን የሚያመጡ እንደ ጨብጥ የመሳሰሉ እና ሌሎች የአባላዘር በሽታወች አጋላጭ ነገሮች
    • አዲስ ወይም ብዙ የፆታዊ ግንኙነት ጓደኛ
    • ኮንደምን ባግባቡ አለመጠቀም
    • አልኮል እና ሌሎች ሱሶችን መጠቀም ወዘተ…
      ሲሆኑ ምልክታቸው ሽንት ሲሸና ከባድ ማቃጠል: ቢጫ ከለር ያለው ሽታ ያለው በዛ ያለ ፈሳሽ ነው
  2. በፆታዊ ግንኙነት የማይተላለፋ ካንዲዲያሲስ የሚባል ፋንገስ እና ባክቴሪያል ቫጂኖሲስ የሚባሉ ከማህፀን ጫፍ ውጪ የሚከሰቱ ኢንፌክሽኖች አጋላጭ ነገሮች
    • ቶሎ ቶሎ ማህፀንን መታጠብ
    • በማህፀን የሚቀመጥ የወሊድ መከላከያ ሲኖር
    • ውፍረት
    • ፆታዊ ግንኙነት ሲበዛ
    • ፀረ ባክቴሪያ መድሀኒቶችን ቅርብ ጊዜ መጠቀም
    • ጥብቅ ያለ የውስጥ ልብስ ፖንት አብዝቶ ማረግ
    • ስኳር ኤች አይ ቪ እና ሌሎች የሰውነት መከላከያ የሚቀንሱ ህመሞች
    • ሲጋራ ማጨስ
      _ ላክቶ ባሲለስ በብዛት የማህፀን ፈሳሽ ውስጥ የሚገኝ ባክቴሪያ ሲሆን አሲድ በማመንጨት ሌሎች ጎጂ ተህዋሲያን እንዳይራቡ ያደርጋል
      _ ከላይ የጠቀስናቸው አጋላጭ ነገሮች ሲኖሩ ግን የባክቴሪያው መጠን ስለሚቀንስ ሌሎች ጎጂ ባክቴሪያወች ሲራቡ ባክቴሪያል ቫጂኖሲስ የሚባል ጤናማ ያልሆነ ፈሳሽ የሚያመጣ ህመም ይመጣል
      *ምልክቱም ማሳከክ የሌለው ነጣ ቀጠን ያለ የአሳ ሽታ ያለው ፈሳሽ ነው
      _ ካንዲዳ አልቢካነስ የሚባል ፋንገስ በተወሰነ ደረጃ መሀፀን ውስጥ ይገኛል
      *ከላይ የጠቀስናቸው አጋላጭ ነገሮች ሲኖሩ ፋንገሱ በብዛት በመራባት ካንዲዲያሲስ የሚባል ኢንፌክሽን ያመጣል
      *ምልክቱም ማሳከክ እና ወፍራም ነጭ እርጎ የመሰለ ፈሳሽ ነው
      _ እንደ ማጠቃለያ ጤናማ ያልሆነ የማህፀን ፈሳሽ በሚኖርበት ጊዜ በግንኙነት የሚተላለፍና የማይተላለፍ ሊሆን ይችላል::
      ዶ/ር ዳዊት ዮሀንስ
      የቆዳና የአባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት
      ጥላ የቆዳና የአባላዘር ህክምና ልዩ ክሊኒክ
      አድራሻ ቦሌ ቡልቡላ ማሪያም ማዞሪያ ፀሀይ ህንፃ ስልክ 0912050354 / 0967253625

Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *