ሶሪያሲስ

ሶሪያሲስ

  • በትክክል ምንነቱ የማይታወቅ የቆዳ መቆጣት የሚያመጣ የቆዳ በሽታ ነው
  • ከበሽታው ጋር ሊገናኙ ወይም ሊያባብሱ የሚችሉ ግን ብዙ ምክንያቶች አሉ
    _ በዘር ወይም በቤተሰብ ተመሳሳይ ችግር ካለ
    የተለያዩ መድሀኒቶች በተለይም ለአእምሮ ህመም ለወባ እና ለደም ግፊት የሚሰጡ መድሀኒቶች አልኮሆል ሲጋራ መጠቀም
    _ ከባድ ሀሳብ ወይም ጭንቀት
    _ ውፍረት
    _ ኤች አይ ቪ እና ሌሎች ኢንፌክሽኖች
    _ እርግዝና
    ምልክቶች
  • ከደህናው ቆዳ በግልፅ የተከለለ ከላይ በጣም ነጭ የሆነ የሚፈረፈር ነገር ያለው ውስጡ ግን በጣም ቀይ ሆኖ ቆዳ ላይ የሚወጣ በሽታ ነው
  • በብዛት የሚወጣው ክርን ላይ: ጉልበት ላይ: ጭንቅላት ላይ: የታችኛው የጀርባ ክፍል ላይ እና ጥፍር ላይ ነው
    ህክምና
  • በተቻለ መጠን ቆዳ ላይ የወጣውን ነገር አለመፈንቀል አለመነካካት
  • ከላይ የተዘረዘሩትን አጋላጭ ነገሮች ማስተካከል
  • በሽታው ስለሚመላለስ ክትትል ማድረግ
  • ቫዝሊን እና ፓራፊን መቀባት
  • የተለያዩ የሚቀቡ እና የሚዋጡ መድሀኒቶች ይኖራሉ
    ዶ/ር ዳዊት ዮሀንስ
    የቆዳና የአባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት
    ጥላ የቆዳና የአባላዘር ልዩ ክሊኒክ
Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *