አስደሳች ዜና ላብ ለሚያስቸግረው
ከመጠን ያለፈ ላብ (hyperhydrosis)
- ከሙቀት ወይም እንቅስቃሴ ጋር የማይገናኝና በብዛት በማላብ ልብስን ወይም እጅን በላብ መዝፈቅ ነው
ምክንያቶች - ከልጅነት ጀምሮ እስከ 24 ዓመት የሚከሰት ከሆነ ያለ ምንም ምክንያት ሊከሰት ይችላል
- ከ30- 50 % ጊዜ በቤተሰብ ተመሳሳይ ችግር ሊኖር ይችላል
- ከ25 ዓመት ቡሀላ የሚከሰት ከሆነ ግን ብዙ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ
_ የስኳር ህመም ኤች አይ ቪ
_ ቲቢ በተለይ ላቡ ማታ የሚብስ ከሆነ
_ የታይሮይድ እና አድሬናል ዕጢ ችግር
_ ማረጥ
_ የልብ ህመም አንዳንድ ካንሰሮች
_ የነርቭ በሽታ ወይም መጎዳት
_ መድሀኒቶች በተለይ ለድብርት ለህመም ማስታገሻ የሚሰጡ
አይነቶች - እጅ እግር ብብት ወይም ፊት ላይ የተወሰነ ሊሆን ይችላል
_ ብዙ ጊዜ ያለ ምንም ምክንያት ይከሰታል - ሙሉ ሰውነት ላይ ሊከሰት ይችላል
_ ከላይ ከተዘረዘሩት አንዱ ሊያመጣው ይችላል
ህክምና - የሚቀባ የሚቀመም እና የሚዋጡ መድሀኒቶች አሉ
- አልሙኒየም ያላቸው ዲዎድራንቶችን መጠቀም
- ቅመማቅመም ሽንኩርት የበዛበት ምግብ መቀነስ በተለይ ከላቡ ጋር ሽታ ካለ
- ካፌይን ያላቸው እንደ ሻይ ቡና መቀነስ
- ሰውነትን ቶሎ ቶሎ መታጠብ
- ከጥጥ የተሰሩ እና ቀለል ያሉ የሚያናፍሱ ልብሶችን መልበስ
- በአዮንቶፎረሲስ በሚባል መሳሪያ ላብን ማከም
- በክሊኒካችን ቢመጡ በዘመናዊ iontophorosis ማሽን የብብት የእጅ እና የእግር ላብዎትን እናክምዎታለን።
ዶ/ር ዳዊት ዮሀንስ
የቆዳና የአባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት


Add a Comment