photo_2024-12-25_07-56-39

የፊት ቆዳ መሳሳት(rosacea)

  • እስከ 10 % የሚሆኑ ሰወች ላይ ይከሰታል
  • መገለጫወቹ የፊት ቆዳ በተለይ ጉንጭ እና አፍንጫ መቅላት ወይም መጥቆር: ማቃጠል: አልፎ አልፎም ሽፍታና መግል ሊይዝ ይችላል
  • በብዛት የሚከሰተው ሴቶች ላይ: ቀላ ያለ የቆዳ ቀለም ያላቸው ላይ እና ከ30 ዓመት ቡሀላ ነው
                               ምክንያቶች
  • በብዛት ምክንያቱ ላይታወቅ ይችላል
  • ፊት በፀሀይ ጨረር ሲጎዳ
  • ስቴሮይድ መድሀኒቶች እንደ ደርማላር ደርሞቬት የመሳሰሉትን መቀባት
                                አባባሽ ነገሮች
  • ሙቀት: ፀሀይ: የሚያቃጥሉ እና ቅመማ ቅመም የበዛባቸው ምግቦች: አልኮሆል: ንዴት: ንፋስ: የመሳሰሉት
  • አልፍ አልፍ ለማድያት ተብሎ የሚቀመሙ መድሀኒቶች ውስጥ የሚጨመሩ መድሀኒቶች
                               ህክምና
  • ፀሀይ መከላከል: የፀሀይ መከላከያ እና ጥላ መጠቀም
  • የፀሀይ መከላከያ ከኬሚካል ይልቅ ፊዚካል ወይም ሚኒራል ሰን ስክሪን መጠቀም
  • ከላይ የተገለፁትን አባባሽ ነገሮች መቀነስ
  • በተቻለ መጠን የሚቀባቡ እና ኮስሞቲክስ ነገሮችን መቀነስ
  • ሳሙናወችን በተቻለ መጠን መቀነስ እና አልፎ አልፎ መጠቀም
  • ፊትን ከሳሙና ይልቅ በክሊንሰር መታጠብ
  • የተለያዩ የሚዋጡ: የሚቀቡ እና የሚቀመሙ መድሀኒቶች ይኖራሉ
  • በተለይ አዜላይክ አሲድ 15 % ጄል (azelaic acid 15 % gel) በጣም አሪፍ መድሀኒት ሲሆን ብዙ ቦታ ግን አይገኝም እኛ ጋር መጥተው ማግኘት ይችላሉ::
                    ዶ/ር ዳዊት ዮሀንስ
              የቆዳና የአባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት
            ጥላ የቆዳና የአባላዘር ልዩ ክሊኒክ
      አድራሻ ቦሌ ቡልቡላ ማሪያም ማዞሪያ ፀሀይ ህንፃ

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *