የቆዳ አለርጂ

የቆዳ አስም

  • በብዛት የሚታይ የቆዳ መቆጣት እና የውስጥ አለርጂ ሲሆን ብዙ ጊዜ ገና በልጅነት ዕድሜ ይጀምራል
  • ከአጠቃላይ ህዝብ 20 % የሚሆነው በዚህ ህመም ሊጠቃ ይችላል
    ምክንያቶች/አባባሽ ነገሮች
  • በዘር መጋለጥ
  • በታማሚው ወይም በቅርብ ቤተሰብ ላይ አስም ወይም ሳይነስ ሲኖር
  • በተፈጥሮ ደረቅ እና ቶሎ የሚቆጣ ቆዳ ሲሆን
  • በዋናነት ያለምንም ምክንያት የሚከሰት የውስጥ አለርጂ ሲሆን እንደ እንቁላል: ወተት እና ለውዝ
    የመሳሰሉ ምግቦች አልፎ አልፎ ሊያባብሱት ይችላሉ
  • ቶሎ ቶሎ መታጠብ
  • በጠንካራ ሳሙናወች በተለይ በልብስና በዕቃ ሳሙናወች መታጠብ
  • ቀዝቃዛ እና ደረቅ አየር (የበጋ ወቅት)
  • የሚኮሰኩሱ ልብሶች
  • ላብና ሙቀት
  • ኢንፌክሽኖች
    ምልክቶች
  • ከፍተኛ የሆነ ማሳከክ
  • ጥፍት ምልስ ማለት
  • ደረቅ ቆዳ
  • የቆዳ ሽፍታወች: የቆዳ መቅላት: የቆዳ ማዠት
  • እየቆየ ሲሄድ የቆዳ መወፈር እና መጥቆር
  • ኢንፌክሽን ሲይዝ መግል መፍሰስ
  • ከ2 ዓመት በታች በሆኑ ህፃናት ላይ የሚወጣው ፊት: ጭንቅላት: ጀርባ: እጅ ወይም እግር ላይ ሲሆን
  • ከፍ ያሉ ህፃናት እና አዋቂወች ላይ መተጣጠፊያ ላይ ይወጣል
    ህክምና
  • በሽታው አለርጂ ስለሆነ ሊመላለስ እንደሚችል እና ህመሙን መቆጣጠር እንጂ ሙሉ ለሙሉ ማጥፋት እነደማይቻል ማስረዳት
  • የቆዳ ቅባቶች እንደ ቫዝሊን: ፓራፊን ወይም ሌሎች ኦይሎችን በየቀኑ መቀባት
  • ሰውነት መታጠብን መቀነስ
  • ወዛማ የሆኑ እንደ ዶቭ ወይም ጆንሰን ያሉ ሳሙናወችን ወይም ሻወር ጄል ለገላ መጠቀም
  • ከጥጥ የተሰሩ ለስላሳ ልብሶችን መልበስ
  • ልብስ ከታጠበ ቡሀላ በደንብ ማለቅለቅ
  • ላብና ሙቀት እንዳይፈጥር ልብስ አለመደራረብ
  • የሚያባብሰው ምግብ ካለ ደጋግመን አይተን እርግጠኛ ስንሆን ነው ማቆም ያለብን
  • የቆዳ ሀኪም ጋር ክትትል ማድረግ
  • የተለያዩ የሚቀቡ እና የሚዋጡ መድሀኒቶች ይኖራሉ
  • ኢንፌክሽን ካለ ማከም
  • ለአለርጂ የምንወስዳቸው መድሀኒቶች የጎንዮሽ ጉዳት ስለሚያስከትሉ በሀኪም ትዕዛዝ ብቻ መወሰድ ይኖርባቸዋል
    ዶ/ር ዳዊት ዮሀንስ
    የቆዳና የአባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት
Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *