1000006867

ከመጠን ያለፈ ላብ

አስደሳች ዜና ላብ ለሚያስቸግረው
ከመጠን ያለፈ ላብ (hyperhydrosis)

  • ከሙቀት ወይም እንቅስቃሴ ጋር የማይገናኝና በብዛት በማላብ ልብስን ወይም እጅን በላብ መዝፈቅ ነው
    ምክንያቶች
  • ከልጅነት ጀምሮ እስከ 24 ዓመት የሚከሰት ከሆነ ያለ ምንም ምክንያት ሊከሰት ይችላል
  • ከ30- 50 % ጊዜ በቤተሰብ ተመሳሳይ ችግር ሊኖር ይችላል
  • ከ25 ዓመት ቡሀላ የሚከሰት ከሆነ ግን ብዙ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ
    _ የስኳር ህመም ኤች አይ ቪ
    _ ቲቢ በተለይ ላቡ ማታ የሚብስ ከሆነ
    _ የታይሮይድ እና አድሬናል ዕጢ ችግር
    _ ማረጥ
    _ የልብ ህመም አንዳንድ ካንሰሮች
    _ የነርቭ በሽታ ወይም መጎዳት
    _ መድሀኒቶች በተለይ ለድብርት ለህመም ማስታገሻ የሚሰጡ
    አይነቶች
  • እጅ እግር ብብት ወይም ፊት ላይ የተወሰነ ሊሆን ይችላል
    _ ብዙ ጊዜ ያለ ምንም ምክንያት ይከሰታል
  • ሙሉ ሰውነት ላይ ሊከሰት ይችላል
    _ ከላይ ከተዘረዘሩት አንዱ ሊያመጣው ይችላል
    ህክምና
  • የሚቀባ የሚቀመም እና የሚዋጡ መድሀኒቶች አሉ
  • አልሙኒየም ያላቸው ዲዎድራንቶችን መጠቀም
  • ቅመማቅመም ሽንኩርት የበዛበት ምግብ መቀነስ በተለይ ከላቡ ጋር ሽታ ካለ
  • ካፌይን ያላቸው እንደ ሻይ ቡና መቀነስ
  • ሰውነትን ቶሎ ቶሎ መታጠብ
  • ከጥጥ የተሰሩ እና ቀለል ያሉ የሚያናፍሱ ልብሶችን መልበስ
  • በአዮንቶፎረሲስ በሚባል መሳሪያ ላብን ማከም
  • በክሊኒካችን ቢመጡ በዘመናዊ iontophorosis ማሽን የብብት የእጅ እና የእግር ላብዎትን እናክምዎታለን።
    ዶ/ር ዳዊት ዮሀንስ
    የቆዳና የአባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት

Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *